Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ከ440 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ እየተከፋፈለ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ከ440 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ የትምህርት ቁሳቁስ እያከፋፈለ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር)÷ የትምህርት ቁሳቁሱን የማከፋፈል ሂደት አሁን ላይ ከመቀሌ መጀመሩን በመግለጽ በቀጣይም ወደተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች እንደሚዳረስ ተናግረዋል።

ድጋፉ የተማሪዎች እና የመምህራን ወንበርን፣ ኮምፒውተር እና ሌሎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ያካተቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍ በበርካታ ትምህርት ቤቶች ያለውን የከፋ የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መገለጹን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በሰሜኑ ጦርነት በትምህርት ቤቶች ያጋጠመው ውድመት ከባድ በመሆኑ ሌሎችም የዚህን አርአያ በመከተል ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.