በገንዳ ውሃ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በድጋፍ ሰልፈኞቹ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራችን ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና የበኩላችንን እንወጣለን፣ በጥቂት ፅንፈኛ ኃይሎች አስተሳሰብና እኩይ ድርጊት የሚበተን ሀገርና ህዝብ የለንም፣ ሀገራችንን ወደ ከፍታ ለማሻገር ከለውጡ አመራር ጋር በፅናት እንቆማለን! የሚሉና ሌሎች ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፉ መልዕክቶች እየተስተጋቡ እንደሚገኙ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡