Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዒድ ሶላት ስነ-ስርአት በፍቅርና በአብሮነት እንዲከበር ላስተባበሩ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ሶላት ስነ-ስርአት በፍቅርና በአብሮነት እንዲከበር ላስተባበሩ አካላት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቀረቡ።

የዒድ አልፈጥር የሶላት ስነስርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ የ1 ሺህ 445ኛዉ የዒድ አልፈጥር በዓል በፍቅርና በአብሮነት በድምቀት ተከብሯል ብለዋል።

ይህን ላስተባበራችሁ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.