Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጀመሪው የዓለም የሥነ-ጥበብ ቀንና የጃዝ ሙዚቃ ቀን ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪው የዓለም የሥነ-ጥበብ ቀን እና የኢትዮጵያ ጃዝ ሙዚቃ ቀን ሊካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮው ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር በዓለም ለስድስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መርሐ ግብሩን ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሠርፀ ፍሬስብሐት አስታውቀዋል፡፡

ኃላፊው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ÷ ቀኑን በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በማክበር በቀጣይ የሚኖረውን የኪነ-ጥበብ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ብሎም የሙዚቃውን ዕድገት ለማገዝና ስለ ሀገራችን መልካም ዕይታን ለመፍጠር መሆኑን አንስተዋል፡፡

ዕለቱ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች እንደሚካሄድ በመግለጽ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ የስዕል ዓውደ ርዕይ፣ የግጥምና የጃዝ ሙዚቃ ኮንሰርትም እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያን ሥነ-ጥበብ ሂደት ለማስተዋወቅ የተመረጡ የሥዕል ስራዎች ለእይታ እንደሚቀርቡም መገለጹን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.