አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የወደፊት የሀገራችን ችግር መፍቻ ቁልፍ ነው – ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የወደፊት የዓለማችን እና የሀገራችን ችግር መፍቻ ቁልፍ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ደስታ የተሰኘች ሮቦት በኢትዮጵያ በመገኘት የሙዚቃ ዝግጅቷን ከአርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ(ዶ/ር) ጋር እያቀረበች እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ፥ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በየጊዜው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያመጣ ኢትዮጵያን ከሌላው ዓለም እኩል እንድትጓዝ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
አያይዘውም ፥ ኢንስቲትዩቱ የወደፊት የዓለም ተፅእኖ ፈጣሪ ታዳጊዎችን ለመፍጠር እየሰራ ያለውን ስራ በዲጂታል ኢትዮጵያ ምክር ቤት ስም ማስገናቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡