Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ የሚከናወኑ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ ህዝብን ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በከተማው በሚገኙ ወረዳዎች ባለፈው አንድ ወር በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ለድጋፍና ክትትል ከተመደቡ አመራሮች ጋር ባደረጉት በውይይት ላይ እንደገለጹት÷ ህዝብን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል።

በተለይም የአረንጓዴ ልማትና የከተማ ፅዳትና ውበት ስራዎች ሐረርን ለነዋሪዎቹ ምቹና በጎብኚዎች ተመራጭ ከተማ ለማድረግ እንደሚቻል ያመላከተ ነው ብለዋል።

በጽዳትና ውበት፣ በደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ በአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ በህገ ወጥ ንግድና ግንባታ እንዲሁም በመንገድ ዳር መብራት ስራዎች ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አመራሩ በቅንጅት በመስራቱ ውጤት ማምጣቱን ጠቅሰው÷ በቀጣይም እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በቀጣይም ተቋማት ስራዎቹ ዘላቂ እንዲሆኑ ለማድረግ መረባረብ ይገባቸዋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም የጁገል ዓለም አቀፍ ቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.