Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት የእጅ ኳስ ውድድርን ከግንቦት 4 ጀምሮ ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ዞን አምስት የእጅ ኳስ ውድድርን ከግንቦት 4 ጀምሮ  እንደምታስተናግድ ተገለፀ፡፡

በአለም የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን እና በአፍሪካ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን በጣምራ የሚዘጋጀው ውድድሩ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከግንቦት 4 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሏል።

ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ፣  ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ታንዛንያና ዩጋንዳ በውድድሩ ይካፈላሉ ተብለው የሚጠበቁ  ሀገራት ናቸው።

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የዞን አምስት የታዳጊዎች የእጅ ኳስ ውድድርን በ2006 ዓ.ም ማስተናገዷ የሚታወስ ነው።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.