Fana: At a Speed of Life!

ከቀበና እስከ መገናኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ሥራ 98 በመቶ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቀበና ድልድይ እስከ መገናኛ ዳያስቦራ አደባባይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ሥራ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ሥራ 98 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በዚህ የመስመር የማዛወር ስራ 3 ነጥብ 75 ኪ.ሜ መካከለኛ መስመር፣ 4 ነጥብ 1 ኪ.ሜ የዝቀተኛ መስመር፣ 16 ትራንስፎርመሮችና 3 ስዊቺንግ ስቴሽኖችን ቀድሞ ከነበሩበት በማንሳት ወደ ተመደበላቸው ቦታ ማዛወር ተችሏል፡፡

በማዛወር ሥራውም 103 አዲስ የኮንክሪት ምሰሶዎች፣ 100 አዲስ የእንጨት ምሰሶዎች፣ አንድ ድራም የኤሌክትሪክ ኬብል እና 200 ሜትር የከፍተኛ ቮልቴጅ የመሬት ውስጥ ኬብል ከነባሩ በተጨማሪ ጥቅም ላይ መዋሉ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም 98 ነባር የኮንክሪት ምሶሶዎችን የማንሳትና አንድ ስዊቺንግ ስቴሽን በአዲስ ለመቀየር እየተሠራ ነው መባሉን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የማዛወር ሥራ ሲከናወንም በአካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.