ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሣይንስ ሙዝየም የተከፈተውን የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይን ጎብኝተዋል፡፡
ምክትል ጠቀላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷ የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይው በተለያዩ ዘርፎች ትላልቅ ኃሳቦች፣ ትልሞች፣ ዲዛይኖች፣ ሞዴሎች፣ የምርት ሙከራዎችእንዲሁም ምርቶች የታዩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህም ሀገራችን በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ለመሆን ትክክለኛ መንገድ ላይ ስለ መሆኗ ማሳያነው ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በተጨማሪም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ተገኝተዋል።
መጋቢት 30 በጀመረው እና እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ ከ900 የሚልቁ ስታርት አፖች ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩ እና ወደገበያ የመቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ ስታርት አፖችም ሥራዎቻቸውን ለዕይታ አብቅተዋል።
በይስማው አደራው