Fana: At a Speed of Life!

አትሌት መዲና ኢሳ በ5 ኪሎ ሜትር ከ20 ዓመት በታች የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲዳስ ኩባንያ ባዘጋጀው አዲዜሮ የ5ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡

የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና ርቀቱን 14 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ጭምር ያሸነፈችው፡፡

በዚሁ ውድድር አትሌት መልክናት ውዱ ሁለተኛ እንዲሁም ፎቲየን ተስፋይ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ዮሚፍ ቀጀልቻ በ13 ደቂቃ በመግባት ሲያሸንፍ ይሁኔ አዲሱ በ5 ሴኮንዶች ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.