Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን በመረዳት የሀገር ደህንነትን የሚያስጠብቁ መሪ መኮንኖችን እያፈራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ እንደተቋም ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን በመረዳትና በመተንተን ሀገራዊ ደህንነትን የሚያስጠብቁ መሪ መኮንኖችን እያፈራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያሰለጠናቸዉን ከፍተኛ መኮንኖች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

መከላከያ እንደተቋም አለም አቀፍና አህጉራዊ ብሎም ቀጠናዊ ሁኔታዎችን አስቀድሞ በመረዳትና በመተንተን ሀገራዊ ደህንነትንና ጥቅምን የሚያስጠብቁ የተማሩና የሰለጠኑ መሪ መኮንኖችን እያፈራ መሆኑን የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ምክትል ሃላፊ ሜጀር ጀኔራል ሰለሞን ቦጋለ ገልፀዋል፡፡

ጀኔራል መኮንኑ የሀገር ስላምና ደህንነት የሚረጋገጠዉ የሰለጠነና በሁለንተናዊ ብቃቱ የተሟላ እዉቀት ያለዉ የጦር መሪ ሲኖር መሆኑን ገልፀዉ ፥ ይህን ለማሳካት ኮሌጁ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለዉ አሥረድተዋል፡፡

ሜጄር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከመደበኛ ግዳጁ ባሻገር የአመራሩን አቅም ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን የዛሬ ተመራቂዎች ምሳሌ ናቸዉ ብለዋል የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ተክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል አበበ ዋቅሹም፡፡

በየወቅቱ እየተቀያየረ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሆነዉን ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ስጋቶችን ለማስወገድ በእዉቀት የበለፀጉ መሪ መኮንኖችን ማፍራት ተገቢ መሆኑን የገለፁት የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋድር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ናቸዉ፡፡

ብርጋዲየር ጄኔራሉ ፥ ኮሌጁ ከመደበኛ ስልጠናው በሻገር መምህራኖቹን በማንቀሳቀስ የአመራር ስልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ለአካዳሚ ዲን ኮሎኔል ጥላሁን ደምሴ ተመራቂ አመራር መኮንኖቹ በስልጠና ቆይታቸዉ ተለዋዋጭ በሆነዉ ሀገራዊ አከባቢያዊና አለም አቀፍ የደህንነት ሁኔታ በመተንተን ብሄራዊ ጥቅሞችንና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች እንዲሁም ስጋቶችን መለየት የሚያስችል የትንተና እዉቀትና ክህሎት መፍጠራቸዉን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.