Fana: At a Speed of Life!

 ኢትዮጵያና የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ትብብራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ኮሚሽነር ተወካይ ማርሴል ክሌመንት አክፖቮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ምስጋኑ መንግስት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡

መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡

ማርሴል ክሌመንት በበኩላቸው ተቋማቸው በኢትዮጵያ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግስትን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.