Fana: At a Speed of Life!

በአቡዳቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ሠራተኞች ለጽዱ ኢትዮጵያ የ252 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቡዳቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን በመቀላቀል የ252 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡

ከሚሲዮኑ ዲፕሎማቶች 160 ሺህ ብር እንዲሁም ከአቡዳቢ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ሰራተኞች 92 ሺህ ብር መሰብሰቡን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) ÷በቀጣይ በአቡዳቢና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በንቅናቄው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል፡፡

በሰባቱም ኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጎ ምላሽ በመስጠት እንደ ሁልጊዜው ከሀገራቸው ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.