Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ለኢንቨስትመንት የተዘጋጁ መሬቶችን እንዲሁም በመልሶ ማልማት ከጁገል ዙሪያ ለተነሱ የገበያ ቦታዎች የተዘጋጁ መሬቶችን እና በሸዋበር ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ስፍራ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አግባብነት ላላቸው አካላት የተዘጋጁ የመሬት ጥያቄ ላይ በስፋት ተወያይቶ አጽድቋል።

ለባለሃብቶች የመሬት ምደባ የተደረገላቸውም ፥ በሚሰማሩበት የልማት መስክ ክልላዊ ፋይዳ ያላቸውና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።

መስተዳድር ምክር ቤቱም የተሰጠው መሬት ለተፈለገው ልማት እንዲውል በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ ማስቀመጡም ነው የተገለጸው።

በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ ማስተላፉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.