Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 262 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 262 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 262 ዜጎች ውስጥ 1ሺህ 261 ወንዶች እና አንድ ሴት ሲሆኑ ፥ ከተመላሾች መካከል 12 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በዓየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለካታል፡፡

ከሚያዝያ 4 / 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ11ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.