Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 44 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሰራ መሆኑንም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.