Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የተመድ ዋና ጸሀፊ ልዩ ተወካይና ዩኤንሶም ሀላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ ልዩ ተወካይና በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ድጋፍ ተልዕኮ(ዩኤንሶም) ሀላፊ ካትሪዮና ላንግ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ታዬ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ቀጣይነት ያለው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

ካትሪዮና ላንግ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ያደረገችውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ የቀጣናውን ሰላም ለማረጋጋት በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.