Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ም/ቤት የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የክልሉ አስፈፃሚ መሥሪያ ቤቶች ሪፖርታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተገኙበት እያቀረቡ ነው።

አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት÷ በመድረኩ በክልሉ ባለፉት በዘጠኝ ወራት ለማከናወን የታቀዱ ስራዎች ይገመገማሉ።

በተለይም ነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በየዘርፉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ መደበኛ ስራዎች ያሉበት ደረጃ በትኩረት ይገመገማል መባሉንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በግምገማ መድረኩ ለህዝቡ የተገባውን ቃል እውን ከማድረግ አኳያ የታዩ ጥንካሬና ድክመቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.