Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሳደግ የሚያስችሉ ውይይቶች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና በዘርፉ አብሮ ለመሥራት የሚያስችሉ የሁለትዮሽ ውይይቶች በዶሚኒካ ሪፐብሊክ ፑንታካና ከተማ ተካሂደዋል፡፡

በዶሜኒካ ሪፐብሊክ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ድርጅት (አይ ሲኤኦ) ሲምፖዚየም ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከተለያዩ ተቋማትና ሀገራት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ድርጅት ሲምፖዚየም ጎንለጎን የድርጅቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ዋና ፀሐፊን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የትራንስፖርትና አቪዬሽን ዘርፍ ሚኒስትሮች እንዲሁም ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል።

በሁለትዮሽ ውይይቶቹ የኢትዮጵያን በአቭዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማስቀጠል በሰው ኃይል ስልጠና፣ በዲጂታላይዜሽን፣ የአየር ናቪጌሽን ቁጥጥር በማዘመን፣ የአውሮፕላን አካላትን ምርት በኢትዮጵያ በማስፋፋት እንዲሁም በአፍሪካ የአየር አገልግሎት ትስስር ለማጠናከር መምከራቸው ተመላክቷል።

የሁለትዮሽ ውይይቶቹ ከካናዳ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ከሲንጋፖር እና ከሴራልዮን የትራንስፖርትና አቪዬሽን ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር የተደረገ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.