Fana: At a Speed of Life!

ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጸሎተ ሐሙስ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡

መስዋዕተ ቅዳሴ፣ የቅባ ቅዱስ ቡራኬና ህፅበተ እግር የዚሁ አካል ሲሆኑ ቀኑ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ትህትናና መተሳሰብን ያስተማረበት መሆኑ ተገልጿል።

በፒያሳ ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴና የቅባ ቅዱስ ቡራኬ እየተካሄደ ነው።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.