Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፥ ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞቻችን እና የከተማ አስተዳደራችን ተቋማት የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ255 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና ለአቅመ ደካሞች በዓሉን በፍሰሐ እንዲያከብሩት ማዕድ አጋርተናል ብለዋል፡፡

ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማዋ ልበ ቀና ባለሃብቶች እና በጎ ፈቃደኞች በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.