Fana: At a Speed of Life!

የኢስላማባድ የንግድ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የቢዝነስና ንግድ ጉዞ እንዲሳተፍ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር እና የኢስላማባድ ፕሬዚዳንት የንግዱ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ በሚካሄደው 2ኛው የቢዝነስና ንግድ ጉዞ እንዲሳተፍ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር በኢስላማባድ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ ፎረም ከፕሬዝዳንቱ አህሳን ዛፋር ባክታዋሪ ጋር በመሆን መርተውታል።

በኢስላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ወደ ኢትዮጵያ በሚደረገው 2ኛው የቢዝነስ እና ንግድ ልኡካን ቡድን የኢስልማባድ የንግድ ማህበረሰብ እንዲሳተፍ ለማድረግ ታስቦ በነበረው የቢዝነስ ፎረም ላይ ከበርካታ ዘርፎች የተውጣጡ የንግዱ ሰዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ አምባሳደር ጀማል በከር እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ መንግስት በአምስቱ ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በግብርናና አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማእድን፣ በቱሪዝም እና በአይሲቲ ከፍተኛ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡

በፎረሙ ከኢስማባድ የንግድ ማህበረሰብ ጋር መድረኮች ይኖራሉ፤ የኢንዱስትሪና አይሲቲ ፓርኮች ጉብኝት ይካሄዳል፤ ከከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ምክክር ይደረጋል፤ አዲስ የተገነቡ የቱሪስት መዳረሻዎች መጎብኘትና የተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩ አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር ለፎረሙ ተሳታፊዎች፥ 6ኛው የአዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ እና ቴክኖሎጂ የንግድ ትርኢት ከፈረንጆቹ ግንቦት 23 እስከ 27 ቀን 2024 በአዲስ አበባ የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ ፎረምን ያካተተ እንደሆነም ነው ያስታወቁት፡፡

“በኢትዮጵያ ሁለተኛውን የቢዝነስ እና የንግድ ልኡካን ቡድን ከመላው አፍሪካ እና ዓለም የተውጣጡ አምራቾች በተገኙበት በአለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ ንግድ ትርኢት ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛሉ” ሲሉም አክለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው ባለፈው ዓመት በተሳተፉበት ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የእንግዳ ተቀባይነትን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም የኢስላማባድ የንግድ ማህበረሰብ በዚህ ፎረም እንዲሳተፍ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.