Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷ያለፉት የፆምና የፀሎት ጊዜያት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መንፈሳዊ ሕይወትን በማደስ ፈሪሃ ፈጣሪን የተላበሰ ስብዕናና ሞራላዊ እሴትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና የተጫወቱ ናቸው ብለዋል።

በየእምነቶቻችን አስተምህሮዎችና ድንጋጌዎች መሠረት የምናከናውናቸው ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ውስጣዊና ውጫዊ ሠላምን በማጎናፀፍ የእርስ በርስ ትስስራችን በፍቅር፣ በመከባበርና በመቻቻል ላይ እንዲመሠረትና እንዲጠናከር ድልድይ ሆነዉ የሚያገለግሉ ናመሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

በፆሙ ጊዜያት ያጎለበትናቸው መልካም ተግባራት የአብሮነትን ድልድይ የሚያጠናክሩ፣ መልካምነትን የሚያላብሱ፣ የመተባበርና የመቻቻል ሠንሰለትን የሚያጎለብቱ በመሆናቸው የዘወትር የምግባርና የተግባር መርሆዎቻችን ሆነው እንዲቀጥሉ ጥረት ማድረግ ይኖርብናልም ነው ያሉት።

በዓሉ የሐሴት፣ የበረከትና የሠላም እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል አቶ እንዳሻው በመልዕክታቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.