Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል መንግስት ለትንሳዔ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መንግስት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም በተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር እንዲያከብር የክልሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

በተያያዘም ህዝበ ክርስቲያኑን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነትን እንዲያጎለብቱ አስገንዝቧል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ ለተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የልማት ተግባራት ስኬት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የክልሉ መንግስት በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንም መልካም ምኞቱን ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.