Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 907 ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ እና የታደሱ 907 ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ለኑሮ አመቺ ያልነበሩ አፍርሰን በአጭር ጊዜ መልሰን የገነባናቸውን እና ያደስናቸውን 907 ቤቶች እንኳን ለትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለን ለነዋሪዎች አስተላልፈናል ብለዋል።

በተጨማሪም አዳዲስ ግንባታዎችን በዛሬው ዕለት እንዳስጀመሩ ነው የገለጹት፡፡

አርጅተው በመፍረስ ላይ የነበሩ ጎስቋላ ቤቶችን አፍርሰን ለዘመናዊ አኗኗር አመቺ በሆነ መልክ በነበሩበት ቦታ ላይ መልሰን የገነባነው በርካታ ልበቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ነው ብለዋል ከንቲባዋ።

የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል ለወገኖች በመድረስ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ የከተማዋ ባለሃብቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ነዋሪዎች እድሉ ተጠቃሚ ስለሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ከንቲባዋ ፥ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት አዲስ አበባን የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.