Fana: At a Speed of Life!

ትንሳኤ በእርቅ የተሞላ የአዲስ ምዕራፍ ማሳያ ነው – ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትንሳኤ በእርቅ የተሞላ የአዲስ ሕይወትና የአዲስ ምዕራፍ ማሳያ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ÷ የትንሳኤን በዓል አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ÷ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቁ የሚከበረው ትንሣኤ በበረከት የተሞላ የአዲስ ህይወትና አዲስ ምዕራፍ ተምሳሌት መሆኑ እንደሚታመን ገልጸዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የተጓዘበት መንገድና ያሳያቸው የፍቅርና የሠላም ድርጊቶች ዝቅ ብሎ ማገልገልን፣ በትዕግስትና በመፈቃቀር ሁሉንም የሰው ልጅ ማክበርን እንደሆነ አውስተዋል፡፡

እነኚህን አስተምህሮዎችን በመከተል “እኛም በዓሉን ስናከብር የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአገልጋይነትን ልቦና ተላብሰን ሊሆን ይገባል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ የብዝሃ ሃይማኖት ተከታይ ህዝቦች ባለቤት እንደመሆኗ ፥ የቆየውን የመቻቻል፣ የመከባበርና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆንም ተመኝተዋል ።

የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ፣ የክልሉ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመደጋገፍ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዓሉን ስናከብር የተራበውን በማብላት፣ የታረዘውን በማልባስ፤ የታመመውን በመጠየቅ ፍቅርና አንድነትን በማሳየት ሊሆን ይገባልም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.