ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 194 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ወገኖችም ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ባለው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራም ከ16 ሺህ በላይ ወገኖችን መመለስ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡