Fana: At a Speed of Life!

83ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) -ኢትዮጵያውያን አርበኞች የጣልያንን ወራሪ ኃይል ድል ያደረጉበት 83ኛው የአርበኞች ድል በዓል አራት ኪሎ በሚገኘው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ኃውልት በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ አባት አርበኞች፣ እናት አርበኞች፣ የአርበኛ ቤተሰቦች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በበዓሉ ላይ ለአርበኞች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.