Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ትናንት ምሽት ላይ በእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የትንሳኤ በአል ዋዜማ ምሽት ላይ በእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የመዲናዋ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ማሪያም ማዞሪያ አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአደጋው ምክንያት ደግሞ በጀነሬተር ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም በዋዜማው ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ የኤሌክትሪክ መቋረጥ በማጋጠሙ ነዳጅ ጨምሮ ጄነሬተር ለማስነሳት ሲሞክር የነበረው የ26 አመቱ ወጣት በእሳት አደጋው ወዲያዉ ህይወቱ ማለፉን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር በስፋራው ደርሰው በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከተል እሳቱን መቆጣጠር መቻላቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም ህዝበ ክርስቲያኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ በመጠንቀቅ ሊሆን እንደሚገባ ባለሙያው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.