Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አርሜኒያ በከበሩ ማዕድናት ላይ በጋራ ለመስራት ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና አርሜኒያ በከበሩ ማዕድናት ላይ በጋራ ለመስራት ውይይት አደረጉ፡፡
 
የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) በኢትዮጵያ የአርሜኒያ አምባሳደር ሳሀክ ሳርጊሲያን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በከበሩ ማዕድናት ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አርሜኒያ በማዕድን ልማት ከ100 ዓመታት በላይ የተሻገረ የዳበረ ልምድ ያላት ሀገር መሆኗ ይታወቃል።
 
አርሜኒያ በማዕድን መስክ ልምድ ያላት ስትሆን፤ የአርሜኒያ ጂኦሎጂስቶች በዘርፉ ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃ ያከማቹ፣ ጠንካራ የማዕድን መሠረት የፈጠሩና ከማዕድን ዲዛይን እስከ ብረት ማቅለጥ ድረስ ብዙ የኢንዱስትሪ ቅርንጫፎች ያለሙ ናቸው፡፡
 
በሀገሪቱ የጂኦሎጂካል ፈንድ ውስጥ ከ 100 እስከ 200 ዓመታት እድሜ ያለው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ መረጃ መያዙም ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.