Fana: At a Speed of Life!

የበጀት ጥያቄዎች የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ የተቃኙ ሊሆኑ ይገባል ተባለ

 

 

 

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የበጀት ጥያቄዎች የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ የተቃኙ ሊሆኑ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

 

 

የግብርና ፣ የፍትህ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከነተጠሪዎቻቸው የ2017 የበጀት ዕቅዳቸውን ለገንዘብ ሚኒስቴር አቅርበው ግምገማ ተካሂዶባቸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ÷ ለሚኒስቴሩ የሚቀርቡ ረቂቅ የበጀት ጥያቄዎች የ10 አመቱ መሪ ሀገራዊ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ የተቃኘ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

በዚሁ መሰረትም ሶስቱ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቶችና ተጠሪዎቻቸው የ2017 ረቂቅ የበጀት ዕቅዳቸውን ያቀረቡ ሲሆን÷ በእያንዳንዳቸው ላይ ዝርዝር ግምገማ ከተካሄደባቸው በኋላ ከሚኒስቴሩ የተለያዩ የሰራ ክፍሎች ሙያዊ አስተያየቶች ተሰጥቷቸዋል።

ባለበጀት መስሪያ ቤቶችም የቀረቡላቸውን ዝርዝር አስተያየቶች በግብአትነት አካተው በተቀመጠው ጣራ መሰረት ቁጠባና ውጤታማነትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተከለሰ ዕቅዳቸውን በሶስት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መሰጠቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.