Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ከነገ ጀምሮ የመንግሥት የሥራ ሠዓት ወደ መደበኛው እንደሚመለስ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሙቀት መጠኑ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ ከነገ ጀምሮ የመንግሥት የሥራ ሠዓት ወደ መደበኛው የሥራ ሠዓት እንደሚመለስ የጋምቤላ ክልል መንግሥት አስታወቀ፡፡

የሙቀት መጠኑ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ ለሥራ ምቹ ሁኔታ ስለተፈጠረ የክልሉ የሥራ ሠዓት ከነገ ጀምሮ ወደ ቀድሞው የሥራ ሠዓት እንዲመለስ መወሰኑን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ኦኬሎ ኮም አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ላለፉት ሦስት ወራት ከጠዋቱ 1 ሠዓት እስከ 5 ሠዓት ከ30 የነበረው ከ1 ሠዓት እስከ 6 ሠዓት ከ30 መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም ከሠዓት በኋላ ከ10 ሠዓት እስከ 12 ሠዓት ከ30 የነበረው ከ9 ሠዓት እስከ 11 ሠዓት ከ30 ሆኖ ወደ ቀድሞው እንደሚመለስ መናገራቸውን ክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የመንግሥት ሠራተኞችም በመደበኛ ሠዓት ወደ ቢሮ በመግባት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ሲሉም አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.