Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ9 ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያለፉት ዘጠኝ ወራት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫዎች የአመራር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት÷ መድረኩ የክልሉን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም መገምገምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በጥናት መለየት ነው።

በውይይቱ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች ተለይተው ከዚህ መነሻ የወደፊት ክልላዊ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ገልጸዋል።

በተለይም የህዝብ ተጠቃሚነትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች እና የስራ አመራር ሰጪነት ጉዳዮች በጥልቀት እንደሚገመገሙ ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.