Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የአካባቢ ብክለት መከላከል የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተሾመ አቡኔ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት ተገኝተዋል።

የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄው “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሐሳብ ለ6 ወራት እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

ንቅናቄው በክልሉ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን ለማጎልበትና የማህበረሰብ ተሳትፎ ንቅናቄውን ከግብ ለማድረስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በከተማው እየተካሄደ ባለው ንቅናቄ በአየር፣ ድምጽ፣ ውሃ፣ በአፈርና ሌሎች ብክለቶች እና በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮሩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ በከተማው ንቅናቄውን የሚያበስር ቢል ቦርድ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተመርቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.