Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ውብና ዘመናዊ ከተማ ለመፍጠር የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት የሚያግዙ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሚገነባቸው ዘመናዊ ሕንጻዎችና የመኖሪያ መንደሮች ውበትን፣ ጥራትንና እና ዘመናዊነት ታሳቢ ያደረጉ ግንባታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ላይ አንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይ ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅንናቄ መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.