Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን የበኩሏን እንድትወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ሁሉን አቀፍ የሰላም ማስፈን ሂደት ውስጥ ኢትዮጵያ ወሳኝ ሚናዋን እንድትጫወት ሱዳን ጠየቀች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሱዳን ሪፐብሊክ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አዋድ አሊ መሃመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና በሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደር መሀመድ ሁሴን በወቅቱ÷ ኢትዮጵያ በሱዳን ሁለንተናዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ውስጥ እየተጫወተችው ያለውን ሚና በማድነቅ በሀገራቱ ታሪካዊ እና ወንድማማችነታዊ አጋርነት ላይ የተመሰረተ ወሳኝ ሚናዋን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የሱዳንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ የምትጫወተውን ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ፣ የሱዳን ሁሉን አቀፍ የሰላም ሂደት በሱዳናውያን ባለቤትነትና መሪነት መከናወን አለበት የሚል ፅኑ እምነት እንዳላት መግለፃቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.