Fana: At a Speed of Life!

ለሴቶችና ሕፃናት ኮሚሽነር ለመሾም 213 ሴት ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶችና ሕፃናት ኮሚሽነር ለመሾም በተሰጠው ጥቆማ 213 ሴት ዕጩዎች መጠቆማቸውን ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው አስታወቀ፡፡

የሴቶችና ሕፃናት ኮሚሽነርን ለመሾም የተቋቋመው ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ የዕጩ ምዝግባውን ሂደት ሪፖርት ተመልክቷል፡፡

ዕጩዎች ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች እና የጥቆማ ዘዴዎችን በሚመለከት ሚዲያን ጨምሮ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ መቻሉን ኮሚቴው አስረድቷል፡፡

በዚህም በስልክ፣ በኢ-ሜልና ዋትስአፕ እና በመመዝገቢያ ሳጥንም ጭምር አሳታፊ በሆነ መልኩ ዕጩዎችን መመዝገብ መቻሉን ኮሚቴው ማሳወቁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በቀጣይም ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው በመስፈርቱ መሠረት ዕጩዎችን የመለየት እና የማጥራት ሥራውን በማጠናቀቅ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚጠበቅበት የኮሚቴው ሰብሳቢ አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አስገንዝበዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.