Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ሰላምን ዘላቂ ከማድረግ ጎን ለጎን የልማት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል- አቶ አብዱ ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰላምን ዘላቂ ከማድረግ ጎን ለጎን የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደርና የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ም/ሰብሳቢ አቶ አብዱ ሁሴን ገለጹ።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የሰላምና የፀጥታ ስራዎችን ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ ገምግሟል።

አቶ አብዱ ሁሴን በሰጡት መግለጫ÷ በክልሉ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልሉን ካጋጠመው ችግር ታድጓል ብለዋል፡፡

የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት ባካሄደው ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ በክልሉ ሰላም ማስፈን መቻሉን ነው የተናገሩት።

በዚህም የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ተችሏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ የተገኘውን ሰላም ከህብረተሰቡ ጋር ዘላቂ ከማድረግ ባሻገር የልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡም የጽንፈኞችን ተንኮልና ሀገር የማፍረስ ሴራ በመረዳት ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ሰላሙን በማስከበርና በሌሎችም እያደረገ ያለውን ንቁ ተሳትፎ እንዲያጠናክር አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.