Fana: At a Speed of Life!

አስትራዜኒካ የኮቪድ ክትባት ማምረት ማቆሙን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስትራዜኒካ የኮቪድ ክትባት ምርቶች በጤና ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ተከትሎ ኩባንያው ከዓለም ገበያ መውጣቱን አስታውቋል፡፡

ኩባንያው ይህን የወሰነው አማራጭ የኮቪድ ክትባቶች ወደ ዓለም ገበያ በመምጣታቸው እና የአስትራዜኒካ ክትባቶች የደም መርጋት እንደሚያስከትሉ መረጋገጡን ተክትሎ ነው ተብሏል፡፡

ኩባንያው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በዓለም ከ3 ሚሊየን በላይ ክትባቶችን መሸጡን የገለፀ ሲሆን በዚህም ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮንበላይ ሰዎችን ማዳን መቻሉን አስታውቋል፡፡

ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ በርካታ ክትባቶች መመረታቸውን የገለፀው ኩባንያው÷ ክትባቶቹ ወደ ገበያው መምጣታቸው የአስትራዜኒካ ደንበኞች ፍላጎት እንዲቀንስ ማድረጉን ገልጿል፡፡

አስትራዜኒካ በ2021 የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የዓለም ጤና ድርጅትን እውቅና በማግኘት ክትባቶችን የአውሮፓ ሀገራትን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሲያሰራጭ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ የአስትራዜኒካ ክትባት የደም መርጋት ያስከትላል በሚል የኩባንያው ምርቶች በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ክልከላ የተደረገባቸው ሲሆን ኩባንያው በመጋቢት ወር ከአውሮፓ ሀገራት የገበያ ፈቃዱን ሰርዟል፡፡

ከጎንዮሽ ጉዳት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ክሶች ሲቀርቡበት የቆየው ኩባንያው፣ አሁን ላይ ምርት በማቆም ከዓለም የክትባት ገበያ ለመውጣት መወሰኑን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.