Fana: At a Speed of Life!

 የሐረር ከተማን ለማዘመን ያለመ የደኅንነት ካሜራ መሠረተ-ልማት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐረርን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚያስችል የደኅንነት ካሜራ (ሲሲቲቪ) መሠረተ-ልማት ስምምነት መፈረሙን ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመውም በሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና በኢትዮ-ቴሌኮም መካከል መሆኑን አቶ ኦርዲን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የደኅንነት ካሜራ መሠረተ-ልማት ሥራው በክልሉ የዜጎችን ደኅነት እና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ሐረርን ተመራጭ የጎብኚ መዳራሻ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት፡፡

ሐረርን ለማዘመን በሚደረገው ጥረትም ኢትዮ-ቴሌኮም ላደረገው የቴክኖሎጂ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.