Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 355 ኪሎ ሜትር የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ጽዳትና ጥገና ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 355 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ጽዳትና ጥገና ሥራ መከናወኑን የከተማው መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎች አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም በግንባታ ግብዓትና ተረፈ-ምርት ማጓጓዝ ሂደት በፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ላይ በሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ የሚያስከትለው ጎርፍ የትራፊክ እንቅስቃሴን እያስተጓጎለ ይገኛል ተብሏል።

ችግሩን ለመፍታት ባለስልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 355 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ጽዳትና ጥገና ሥራ ማከናወኑን ነው የገለጸው፡፡

በተጨማሪም ከእሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የሚላኩ ጥቆማዎችን ጨምሮ የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸውን ሥፍራዎች አካቶ የማስተካከያ ሥራዎች እያከናወነ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ አካባቢዎች መካከል ጥበቡ ሰፈር ድልድይ፣ አንፎ ድልድይ፣ ማዘር ትሬዛ ድልድይ፣ የገልማ አባ ገዳ ሰፈር ድሬኔጅ፣ ገላን ኮንዶሚኒየም እና ሌሎች አካባቢዎችም እንደሚገኙበት ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.