Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ተግባራዊ ማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑ ተመላከተ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝቦች መካከል መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን ተግባራዊ ማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ ገለፁ።

ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

በመድረኩ ወ/ሮ ባንቻየሁ ድንገታ እንደገለፁት÷ የሽግግር ፍትሕ በሕዝቦች መካከል መተማመንና ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ ነው።

የሽግግር ፍትሕ በአግባቡ ሲተገበር ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የተሻለ ነገን መፍጠር የሚችል እንዲሁም ትኩረቱን ልማት ላይ የሚያደርግ እና ቅራኔ የሌለው ማኅበረሰብ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ለሽግግር ፍትሕ ውጤታማነት የአመራሩ፣ የምሁራን፣ የሚዲያ እንዲሁም የኅብረተሰቡ ሚና ከምንጊዜውም በላይ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሽግግር ፍትህ ግጭቶችን ለመፍታትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው በመድረኩ መገለፁን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም የሰብዓዊ መብት መከበርን ለማረጋገጥ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.