Fana: At a Speed of Life!

የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተግዳሮቶች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ፡፡

የምክር ቤቱ የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተግዳሮቶች፣ መውጫ መንገዶችና የሕግ አውጪ ሚና በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በፓናሉ ላይ አፈ ጉባዔው÷ የመንግሥት ከ60 በመቶ በላይ የካፒታል በጀት የሚፈስበትን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተግዳሮቶች ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው እና ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

መንግሥት ዘርፉን ለማዘመን ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ጠቅሰው÷ የዘርፉን ችግሮች ለመቅረፍ ተቀራርቦ መሥራትና የመፍትሔ ሀሳብ ማመንጨት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ÷ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን መለየት፣ የመውጫ መንገዶች ማመቻቸት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የህግ አውጪውን ሚና በመለየት በቅንጅት በመስራት  ውጤት ማስመዝገብ የሚቻልበትን አቅጣጫ ማመላከት የፓናል ውይይቱ ዓላማ ነው ማለታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.