Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤ መካሔድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ዓመታዊ የፋይናንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ ጀምሯል፡፡

ለ7ኛ ጊዜ በሚካሄደው የፋይናንስ ጉባኤ÷የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱን ጨምሮ የባንክ ሀላፊዎች፣ የኢንሹራንስ ተቋማት ተወካዮችና የፋይናንስ ዘርፍ ተዋናዮች ተገኝተዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል ምጣኔ ሀብትን መገንባት፣ ትስስርን መፍጠር ፣ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ጨምሮ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረግ የጉባኤው የውይይት አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን በማቋቋም ምህዳሩን ምቹ ለማድረግ እያከናወነች ያለው ተግባርና ይዞት የሚመጣው እድል በጉባኤው እንደሚቀርብም መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጉባኤው የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦችን ለመጠቆም፣ የገበያ ዕድሎችን ለመጠቀም፣ በቀጣናው እንዲሁም በአህጉሩ የፍይናንስ ዘርፍ ምህዳርን ምቹ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የመምከር አላማ አንግቦ የተቋቋመ ነው።

የምስራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.