Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች አቅማቸውን ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሊያውሉ ይገባል-አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች አቅማቸውን ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ሊያውሉ ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በወልቂጤ ከተማ ከቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶች ጋር እየተወያዩ  ነው፡፡

አቶ እንዳሻው በዚህ ወቅት የወጣቱ ሃይል በከንቱ እንዳይባክን ማድረግ የሁሉም ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀው÷ወጣቱ ወደ ኋላ የሚጎትቱ ጉዳዮችን በመተው ልዩነቶችን በማስታረቅና በመነጋገር መርህ ማመን አለበት ብለዋል፡፡

በተለይም ወጣቱ በጋራ  ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት መቻል አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ  አርዓያ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል ።

እንዲሁም ወጣቱ በሀገረ መንግስት ግንባታ ሁለንተናዊ ተሳትፎው ጠንካራ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ወጣቶች በስራ፣ በጥናት እና ምርምር፣ ምርትን በማሳደግ እንዲሁም በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.