Fana: At a Speed of Life!

ሶማሊያ በህዳሴው ግድብ ላይ የኢትዮጵያን አቋም ትደግፋለች – በኢትዮጵያ የሶማሊያ አምባሳደር አብዲሃኪም

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሶማሊያ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የኢትዮጵያን አቋም እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የሶማሊያ አምባሳደር አብዲሃኪም አብዱላሂ ኦማር ተናገሩ፡፡

አምባሳደሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ የህዳሴው ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ተስፋን የሰነቀ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ግድቡ ለቀጠናው ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ትስስር ምክንያት ሊሆን መቃረቡንም አንስተዋል፡፡

በመጭው ሃምሌ ወር የሚካሄደው የግድቡ ውሃ ሙሌት ጊዜውን የጠበቀ እና ተቀባይነት እንዳለው ያነሱት አምባሰደሩ ሙሌቱ በታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ እንደማይኖረውም አስረድተዋል፡፡

ሶማሊያም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሃብት የመጠቀም መብት እንደምታከብርም ገልፀዋል፡፡

ከዚህ አንፃርም ሃገራቸው የኢትዮጵያን እና የቀጠናውን ፤ ብሎም የአፍሪካን ጥቅም በተፃረረ መልኩ የአረብ ሊግ እና ግብፅ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያሳለፉትን ውሳኔም ውድቅ ማድረጓን አውስተዋል፡፡

ሶማሊያ ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያያዘ የኢትዮጵን አቋም መደገፏም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን አካሄድ የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አምባሳደሩ የአከባቢው ሃገራት ከህዳሴው ግድብ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቅሰው ግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ የያዘችው አቋም ተጠቃሚነትን የማያረጋግጥ እና ጠብ አጫሪነት እንደሆነም ነው ያስረዱት፡፡

ሃገራቸውም ተጠቃሚነቷን በማመን የአረብ ሊግን ውሳኔ እና አቋም መቃወሟንም አስገንዝበዋል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.