Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ለተያዘው የ10 አመት መሪ የልማት እቅድ ውጤታማነት የሲቪክ ማህበራቱ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ከሚሽን የተያዘው የ10 አመት መሪ የልማት እቅድ ውጤታማነት የሲቪክ ማህበራቱ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠየቀ::

ኮሚሽኑ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ጋር በመሪ እቅዱ ላይ እየተወያየ ሲሆን፥ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ የ10 አመት መሪ የልማት እቅድን መነሻ፣ ባህሪ እና እቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ አቅሞች ዙሪያ እንዲሁም ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦችን አቅርበዋል፡፡

በዚህም እቅዱ መሰረታዊ የህዝብ ፍላጎቶችን መመለስ በሚችል ደረጃ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ይህ መሪ እቅድ ወጥቶ ወደ ተግባር ሲገባ አዝጋሚ የኢኮኖሚ ለውጥ፣ ለተፅእኖ ተጋላጭ የሆነ ኢኮኖሚ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ አዝጋሚ የኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሽግግር ተግዳሮቶች ተብለው ተቀምጠተዋል፡፡

በመድረኩ በእቅዱ ጥራት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ፣የጋራ ብልፅግና እና በለውጥ ደረጃ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት በትኩረት አቅጣጫነት መቀመጡ ነው የተመለከተው፡፡

የሲቪል ማህበራት ድርጅት ተወካዮች እቅዱ እነሱ ይዘውት የሚንቀሳቀሱትን አላማ የሚደግፍ በመሆኑ ለተፈፃሚነቱ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ተወካዮቹ እቅዱ ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ አብዛኛው ማህበረሰብን የሚዳስስ መሆኑን በመድረኩ አንስተዋል፡፡

በማህበረሰብ ልማት ላይ እቅዱ ትኩረት ማድረጉ እና ለሰብዓዊ ልማት ቅድሚያ መስጠቱ ጠንካራ ጎኑ ነውም ብለዋል፡፡

በጤና ዘርፉ ላይ ጥራት ከማስጠበቅ እንዲሁም በትምህትር ቤቶች ላይም ከተደራሽነቱ ባሻገር ጥራት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡

ከመልካም አስተዳደር አንፃርም ተቋማት ጠንካራና ፍትሃዊ እንዲሆኑ ይጠበቃል ያሉ ሲሆን÷ ይህም ህዝቡ አመኔታ እንዲኖረው ይረዳል ነው ያሉት፡፡

በሃይለየሱስ መኮንን

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.