Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ሶስት የአፍሪካ ሃገራት በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኬንያ አየር መንገድ ዳግም በሶስት የአፍሪካ ሃገራት የንግድ በረራ ሊጀምር መሆኑ ተገለፀ፡፡

አየር መንገዱ በረራ የሚጀምርባቸው ሃገራትም ጋና ፣ ሴራሊዮን እና ላይቤሪያ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በዚህም በሳምንት አራት ጊዜ ወደ አክራ ፣ በሳምንት ሁለት ጊዜ ወደ ፍሪታውን እንዲሁም ወደ ሞንሮቪያ በረራ እንደሚያደርግ ነው የተገለፀው፡፡

በረራውም መስከረም 16 እና 17 እንደሚጀመር ተነግሯል፡፡

አየር መንገዱ በመጋቢት ወር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር አገልግሎቱን አቋርጦ የነበረ ሲሆን ሀምሌ 15 የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር ነሐሴ 1 2020 ቀንም ወደ ኢትዮጵያ እና ብሪታንያ በረራ በማድረግ ዓለም አቀፍ አገልግሎቱን መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.