Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በኮንስትራክሽን ዘርፍ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዷል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በኮንስትራክሽን ዘርፍ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኮንስትራክሽን ዘርፍ የአምስት ዓመት እቅድ እንዲሁም የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱም በዘርፉ በእቅድ ከተያዙት ተግባራት መካከል በቀጣዮቹ ዓምስት ዓመታት 80 በመቶ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ግብዓቶች መተካት፣ በዘርፉ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ስራ እድል መፍጠር፣ በዘርፉ እየታዩ ያሉ የግንባታ ጥራት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችሉ የዳሰሳ ጥናቶችን ማካሄድ ይጠቀሳሉ፡፡
እንዲሁም የውጭ ሀገር ተቋራጮች የሀገር ውስጥ አነስተኛ መለስተኛ እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ተቋራጮችን በማሳተፍ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ማረጋገጥም የእቅዱ አካል መሆኑን ከከተማ እና ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ በአሁኑ ወቅት የኮንስትራክሽን ዘርፉ 25 በመቶ የውጭ ምንዛሪ ወጪ የሚደረግለት እና ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን የካፒታል በጀት የሚወስድ እንደመሆኑ ውጤትን መሠረት ባደረገ እቅድ መመራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች በውጭ ሀገር ተቋራጮች መያዛቸው ከሞላ ጎደል ተወዳዳሪ ሀገር በቀል ተቋራጮች በሚፈለገው ልክ ማፍራት ባለመቻሉ መሆኑን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አሰራር ማሻሻያ ቢሮ ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ተገኝ ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.