Fana: At a Speed of Life!

የሊቢያ የተቀናቃኝ ወገኖች በምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊቢያ ተቀናቃኝ ወገኖች በምርጫው ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

የሃገሪቱ ተፋላሚ ሃይሎች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በጎረቤት ቱኒዚያ የሰላም ድርድር ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በድርድሩም ተፋላሚ ወገኖቹ በ18 ወራት ውስጥ በሃገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸውን በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት መልዕክተኛ ስቴፋኒ ዊሊያምስ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱን የሚታዘብ የሽግግር ጊዜ አስተዳደር ማቋቋምን ያለመ ነው ተብሏል፡፡

መልክተኛዋ በሦስተኛው ቀን የውይይት መጨረሻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሳታፊዎች በ18 ወራት ውስጥ ለሚካሄደው የአካባቢ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ተናግረዋል ፡፡

የሊቢያ ተቀናቃኝ ሃይሎች ባለፈው ወር በጄኔቫ ባደረጉት ውይይት የተኩስ አቁም ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.